እንዳለ ከበደ ወደ መቐለ ከተማ አቀና

መቐለ ከተማ በዝውውር ገበያው በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም እየመራ ይገኛል። እንዳለ ከበደም እለቡን የተቀላቀለ 7ኛ ተጫዋች ሆኗል።

በ2008 አርባምንጭ ከተማን ለቆ ወደ ሲዳማ ቡና ካመራ በኋላ በጉዳት እምብዛም ግልጋሎት ሳይሰጥ ወደ አርባምንጭ ተመልሶ በተለይ ዘንድሮ በግሉ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ችሏል። በአዞዎቹ ውሉን ያጠናቀቀው እንዳለ ወደ ገብረመድልን ኃይሌ መቐለ ከተማ በአንድ ዓመት ውል መቀላቀል ችሏል።

በተጠናቀቀው ዓመት ከአማኑኤል ገብረሚካኤል ውጪ ሁነኛ የመስመር ተጫዋች እጥረት የተስተዋለበት መቐለ ከተማ በእንዳለ መምጣት ቦታውን ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።