የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ረቡዕ የማጣርያ ዝግጅቱን ይጀመራል

በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ረቡዕ በአዋሳ ቅደመ ዝግጅቱን ይጀምራል፡፡

አሰልጣኝ አብሀርም መብራቱ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ተጫዋቾቹም እስከ ነገ ጠዋት በፌዴሬሽን ጽ/ቤት በመገኘት ሪፖርት አድርገው ከሰአት ወደ ሀዋሳ በማምራት ማረፍያውን በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል አድርጎ ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ በይፋ የቅድመ ውድድር ዝግጅት በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም እና በጂም ውስጥ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ በሀገር ውስጥ የሚገኙት ተጫዋቾች ወደ ሀዋሳ እንደሚጓዙ ሲጠበቅ በውጭ ሀገራት ሊጎች ውድድር ላይ የሚገኙት ተጫዋቾች ከነሀሴ 25 በኋላ የሚቀላቀሉ ይሆናል።

በጋና 5-0 ተሸንፎ ጉዞውን የጀመረውና 5 የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚቀሩት ብሄራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ የሜዳ ጨዋታውን ከሴራሊዮን ጋር ጳግሜ 4 ሀዋሳ ላይ ያደርጋል፡፡