ታንዛንያ 2018 | ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ጨዋታዎችን ይመራሉ

በ2019 በታንዛንያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴካፋ ዞን የማጣርያ ውድድር ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ተመርጠዋል፡፡

ከነሀሴ 4-20 በአፍሪካ ዋንጫ ከ17 አመት በታች በሴካፋ የማጣሪያ ቅድመ ውድድር በታንዛኒያ ይደረጋል። በዚህ ውድድር ላይ ከብሔራዊ ቡድኑ ባለፈ ሁለት ኢትዮጽያዊያን ዳኞችም ተካፋይ ይሆናሉ። በዋና ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሰ በረዳትነት ደግሞ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ትግል ግዛው ተመራጮቹ ዳኞች ናቸው፡፡

የ2008 የሊጉ ኮከብ ዳኛ በላይ ታደሰ ዘንድሮ በተለያዩ አህጉራዊ የክለብ ውድድሮች ላይ በመሀል ዳኝነት ሀላፊነት የተሰጠው ሲሆን የዳኞች እና ታዛቢዎች ማህበር ፕሬዘደንት የሆነው ረዳት ዳኛ ትግል ግዛውም በሴካፋ የ17 አመት ውድድር ላይ መዳኘቱ ይታወሳል።