አዳማ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርሟል

አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊጉ በማስፈረም ወደ ቡድኑ የቀላቀላቸውን ተጫዋቾች ቁጥር 5 አድርሷል። ዐቢይ ቡልቲ እና ኄኖክ ካሳሁን ወደ አዳማ ከተማ በሁለት ዓመት ኮንትራት ያመሩ ተጫዋቾች ናቸው።

በግራ መስመር ተከላካይ ስፍራ የሚጫወተው ኄኖክ ካሳሁን ያለፉትን የውድድር ዘመናት በሰበታ ከተማ ያሳለፈ ሲሆን ወደ ትውልድ ከተማው ተመልሷል። በክረምቱ ክለቡን የለቀቀው ሲሳይ ቶሊን ቦታ ይሸፍናል ተብሎም ይጠበቃል። የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ዐቢይ ኢትዮጵያ መድንን ለቆ ወደ ሰበታ ከተማ ያመራው በዓመቱ መጀመርያ ሲሆን በተለይ በመጀመርያው የውድድር ዘመን አጋማሽ ጥሩ አቋም አሳይቷል። በ8 ጎሎችም የሰበታ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነው።

ኄኖክ ካሳሁን

አዳማ ከተማ ከሁለቱ ተጫዋቾች ፊርማ በፊት ቴዎድሮስ በቀለ፣ ሙሉቀን ታሪኩ፣ ሱራፌል ዳንኤልን አስፈርሟል።