አዳማ ከተማ ሐብታሙ ሸዋለምን አስፈርሟል

አዳማ ከተማ ሐብታሙ ሸዋለምን በማስፈረም ወደ ክለቡ የቀላቀላቸውን ተጫዋቾች ቁጥር 5 አድርሷል። 

ሐብታሙ ሸዋለም ወደ አዳማ የሚያደርገውን ዝውውር ዛሬ አጠናቋል። በ2009 አማራ ውሀ ስራን ለቆ ወደ ወልዲያ ያመራው ሐብታሙ በተደጋጋሚ የመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ በመግባት መጫወት ችሏል። የሁለት ዓመት ውሉን ማጠናቀቁን ተከትሎም ከሊጉ የወረደው ወልዲያን በመልቀቅ በሁለት ዓመት ውል ወደ አዳማ አምርቷል።

አዳማ ከተማ በዝውውር መስኮቱ ከሐብታሙ በተጨማሪ ሙሉቀን ታሪኩ፣ ኄኖክ ካሳሁን፣ ዐቢይ ቡልቲ፣ ቴዎድሮስ በቀለን አስፈርሟል።