ፍፁም ተፈሪ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል

በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም ቀዳሚ ከሆኑት ክለቦች አንዱ የሆነው ወላይታ ድቻ ፍፁም ተፈሪን ማስፈረሙን አስታውቋል።

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ከሚሌንየሙ መጀመርያ ወዲህ ብቅ ካሉ ድንቅ አማካዮች አንዱ ሲሆን በሀዋሳ ከተማ (ለሁለት ጊዜያት) ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካሳለፈ በኋላ በ2007 ወደ ሲዳማ ቡና አምርቶ ለአራት ዓመታት ቆይታ ማድረግ ችሏል። በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የለዓለም ብርሀኑ መልቀቅን ተከትሎም የክለቡ የመጀመርያ አምበል የነበረ ሲሆን ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ወላይታ ድቻ በአንድ ዓመት ውል ማምራቱን ክለቡ አስታውቋል።

ወላይታ ድቻ በአጠቃላይ 8 ተጫዋቾችን ሲያስፈርም በአማካይ ስፍራ ክለቡን የለተቀቀው የበዛብህ መለዮን ክፍተት የሚሸፍን ተጫዋች ሳያቀኝ ቆይቶ በመጨረሻ አንጋፋውን አማካይ ማግኘት ችሏል።