መቐለ ከተማ ለሶስት ተጫዋቾች የሙከራ እድል ሰጥቷል

በዝውውሩ መስኮቱ በስፋት የተንቀሳቀሱት መቐለ ከተማዎች አሁን ደግሞ ለቀድሞ ተጫዋቾቻቸው ኃይለዓብ ኃ/ስላሴ ፣ ቢንያም ደበሳይ እንዲሁም በቅርቡ ከእንግሊዝ የተመለሰው አርዓዶም ገ/ስላሴ ሙከራ ሰጥተዋል።

የመሃል አማካዩ ኃይለዓብ ኃ/ስላሴ ወደ መቐለ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ ለ3 ዓመታት ከክለቡ ጋር ቆይታ አድርጎ ደደቢት ቢያቀናም በጉዳት ምክንያት እንደሚፈለገው ደደቢትን ሳያገለግል በድጋሚ ለመቐለ ከተማ እና ለ ወልዋሎ መጫወት ችሎ ነበር። አሁን ለሶስተኛ ጊዜ ወደ መቐለ ለማምራት የሙከራ እድል ተሰጥቶታል።

ሌላው የሙከራ እድል የተሰጠው የአጥቂ ክፍል ተጫዋቹ ቢንያም ደበሳይ ሲሆን በተመሳሳይ ከዚ በፊት ለመቐለ ከተማ መጫወት ችሎ ነበር። ተጫዋቹ ከመቐለ ከተማ  በተጨማሪም በወልዋሎ፣ ወሎ ኮምቦልቻ እና አክሱም ከተማም ቆይታ ነበረው።

የቀድሞው የትራንስ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያ ቡና አጥቂ አርዓዶም ገ/ህይወት ከእንግሊዝ ተመልሶ በመቐለ የሚገኝ ሲሆን የሙከራ እድል ከተሰጣቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው። በእእንግሊዝ ቆይታው በአማተር ሊጎች ውስጥ የተጫወተው አርዓዶም ለቀጣይ ዓመታት የመጫወት እቅድ እንዳለው ለሶከር ኢትዮጵያ መግለፁ የሚታወስ ነው።

ከመቐለ ከተማ ጋር በተያያዘ ዜና በጥር የዝውውር መስኮት ሸባብ ኣል ሳህልን ለቆ መቐለ ከተማን የተቀላቀለው ጋናዊ ኑሁ ፉሴይኒ እና ሌላው ጋናዊ ቢስማርክ አፖንግ ከክለቡ ጋር መለያየታቸው እርግጥ ሆኗል።