የከፍተኛ ሊግ የመለያ እና የዋንጫ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን እና ቦታ ታውቋል

የ2011 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዋንጫ እና ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ወሳኝ የሆነው የመለያ ጨዋታ (Playoff) የሚደረግበት ቦታ ታውቋል።

የከፍተኛ ሊጉ የምድብ ሀ ጨዋታዎች ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቁ የምድብ ለ 30ኛ ሳምንት እና ሶስት ተስተካካይ ጨዋታዎች ይቀራሉ። ፌዴሬሽኑ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ የመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች የሚደረጉበትን ቦታ እና ቀን የወሰነ ሲሆን ነሀሴ 26 የመለያ ጨዋታ፣ ነሀሴ 27 ደግሞ የዋንጫ ጨዋታ በድሬዳዋ እንደሚካሄዱ ታውቋል።

ባህርዳር ከተማ በቀዳሚነት፣ ሽረ እንዳሥላሴ በተከታይነት የምድብ ሀ ውድረርን አጠናቀው ከምድብ ለ አቻዎቻቸው ጋር ጨዋታ ለማድረግ እየተጠባበቁ ሲሆን በቀጥታ ወደ ፕሪምየር ሊግ የሚገባው እና ባህር ዳር ከተማን ለዋንጫ የሚገጥመው ቡድን እንዲሁም በሁለተኝነት አጠናቆ ሽረ እንዳሥላሴን ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ የሚፋለመው ቡድን እስካሁን ያልተለየ ሲሆን በመጪው ነሀሴ 21 በተመሳሳይ ሰዓት ደቡብ ፖሊስ ከ ድሬዳዋ ፖሊስ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከ ጅማ አባ ቡና እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ከ ሀላባ ከተማ በሚያደርጉት የ30ኛ ሳምንት ጨዋታ ይለይለታል።

የመለያ እና የዋንጫ ጨዋታ በድሬዳዋ ሲደረግ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በውድድሩ የሶስት ዓመታት ታሪክ እጅግ ዘግይቶ የሚጠናቀቀው ውድድር የዘንድሮው ሆኗል።

የምድብ ለ ቀሪ መርሐ ግብሮች የሚከተሉት ናቸው:-

30ኛ ሳምንት

ሰኞ ነሀሴ 21 ቀን 2010

ደቡብ ፖሊስ 4፡00 ድሬዳዋ ፖሊስ (ሀዋሳ)

ወልቂጤ ከተማ 4:00 ሀላባ ከተማ (ደቡብ ኮሌጅ ሜዳ)

ሀዲያ ሆሳዕና 4:00 ጅማ አባቡና (ሆሳዕና)

ቡታጅራ ከተማ 6፡00 ካፋ ቡና (ደቡብ ኮሌጅ ሜዳ)

መቂ ከተማ 4፡00 ሀምበሪቾ (መቂ)

ቅዳሜ ነሀሴ 25 ቀን 2010

ቤንች ማጂ ቡና ከ ናሽናል ሴሜንት (ሚዛን አማን)

ረቡዕ ነሀሴ 30 ቀን 2010

ሻሸመኔ ከተማ ከ ስልጤ ወራቤ (ሻሸመኔ)

ዲላ ከተማ ከ ነጌሌ ከተማ (ዲላ)

ተስተካካይ ጨዋታዎች

ረቡዕ ነሀሴ 30 ቀን 2010

ቤንች ማጂ ቡና ከ ድሬዳዋ ፖሊስ (28ኛ)

ናሽናል ሴሜንት ከ ቡታጅራ ከተማ (27ኛ)

ወልቂጤ ከተማ ከ ካፋ ቡና (ከተቋረጠበት የሚቀጥል