ሴቶች ዝውውር | አዳማ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በሴቶች ፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮት ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው አዳማ ከተማ ሶስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አስታውቋል።

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቿ አልፊያ ጃርሶ ደደቢት ባለፉትን ሶስት ዓመታት ተከታታይ ቻምፒዮንነት መደበኛ ተሰላፊ የነበረች ሲሆን የሰማያዊዎቹን ውል አገባዳ ወደ አዳማ ከተማ ማምራቷ ታውቋል። ፋሲካ መስፍን ሌላዋ የክለቡ ፈራሚ ናት። የመስመር ተከላካይዋ እስከተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አሳልፋለች። ሳራ ነብሶን ከጌዴኦ ዲላ ያስፈረመው ክለቡ የተከላካይ መስመር ተጫዋቿ ሀና ኃይሉንም ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

አዳማ ከተማ ካስፈረማቸው 7 አዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ የስምንት ነባር ተጫዋቾችን ውል ማደሱን አሳውቋል። ሴናፍ ዋቁማ፣ መስከረም መንግስቱ፣ ናርዶስ ጌትነት፣ ቤተልሄም አስረሳኸኝ፣ ባንቺዓየሁ ታደሰ፣ ገነት ኃይሉ፣ ዮዲት መኮንን እና እምወድሽ ይርጋሸዋ ውላቸውን ያደሱ ተጫዋቾች ናቸው።