በሀገር አቀፍ የታዳጊዎች ስልጠና ምዘና ውድድር ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉ ክልሎች ታውቀዋል

ከነሀሴ 13 ጀምሮ በአዳማ እየተካሄደ የሚገኘው የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት የምዘና ውድድር የእግርኳስ ዘርፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ የገቡትን ክልሎች ለይቷል። 

በወንዶች የምድብ ጨዋታዎች የተጠናቀቁ ሲሆን በሁለቱ ምድቦች ከተመዘገቡ ውጤቶች በኋላ ያለው የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን መስሏል።

ምድብ ሀ

1. አማራ 4 (+7) 10

2. ደቡብ 4 (+4) 9

———-

3. ድሬዳዋ 4 (+4) 5

4. ጋምቤላ 4 (-2) 4

5. ቤንሻንጉል 4 (-13) 0

ምድብ ለ

1. ኦሮሚያ 3 (+10) 9

2. ሐረር 3 (-1) 3

———-

3. አፋር 3 (-4) 3

4. አአ 3 (-5) 3

በሴቶች ውድድር የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ነገ የሚደረጉ ሲሆን ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉት ቡድኖች ግን ታውቀዋል። ከምድብ ሀ አዲስ አበባ እና ደቡብ ሲያልፉ ከምድብ ለ አማራ እና ኦሮሚያ አልፈዋል። ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ የሁለቱ ምድብ አንደኛ እና ሁለተኛ ይለያሉ።

የግማሽ ፍፃሜ መርሐ ግብር

የወንዶች – ሀሙስ ነሀሴ 24 ቀን 2010

3:00 አማራ ከ ሐረር (አዳማ አበበ ቢቂላ)

5:00 ኦሮሚያ ከ ደቡብ (አዳማ አበበ ቢቂላ)

የሴቶች የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ አርብ ሲደረግ

የፍፃሜ ጨዋታዎች እሁድ እንደሚከናወን ታውቋል።