ሲዳማ ቡና የሶስት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

በዝውውር ገበያው የዘገየ ቢመስልም ኃላ ላይ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ እየቀላቀለ ያለው ሲዳማ ቡና ሶስት ተጫዋቾችን የግሉ አድርጓል፡፡

ለ2011 የውድድር ዘመን ተጠናክሮ ለመቅረብ በርካታ ክለቦች አዳዲስ ተጫዋቾችን እየቀላቀሉ ይገኛሉ በዝውውር መስኮቱ ዘግየት ብሎ ተቀላቅሎ የነበረው ሲዳማ ቡና ከሳምንት በፊት በከፍተኛ ሊግ ወሳኝ ጨወታ ያለባቸውን ሁለት የአማካይ ስፍራ ተጫዋችንና አንድ ግብ ጠባቂን ለሁለት ዓመታት  አስፈርሟል፡፡ 

እግር ኳስን በደቡብ ፓሊስ የጀመረውና በ2008 ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ወደ ፕሪምየር ሊግ አድጎ በክለቡ መጫወት ችሎ የነበረው እንዲሁም በ2009 ዳግም ተመልሶ በቀድሞው ክለቡ በአማካይ ስፍራ በመጫወት ዘንድሮ ደቡብ ፖሊስ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲገቡ ካስቻሉ ተጫዋቾች መካከል አበባየሁ ዮሀንስ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል፡፡ 

ሌላኛው አዲስ ፈራሚ የመስመር ተጫዋች የሆነው ዳዊት ተፈራ ነው። ሻሸመኔ ከተማን በመልቀቅ ላለፉት ሶስት ዓመታት በጅማ አባቡና ጥሩ ጊዜን ያሳለፈውን እና በአሰልጣኝ ግርማ ሀ/ዮሀንስ ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ዳዊት በፍፁም ተፈሪ መልቀቅ የተፈጠረውን የፈጣሪ አማካይ ክፍተት እንደሚሸፍን ይጠበቃል።

በሲዳማ ቡና ከዚህ ቀደም በግብ ጠባቂነት የሚታወቀው አዱኛ ደረጀ ሌላው ክለቡን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው።