አዳማ ከተማ ዐመለ ሚልኪያስን አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ ቀስ በቀስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው አዳማ ከተማ አዳማ ከተማ ከመቐለ ከተማ የለቀቀው ዐመለ ሚልኪያስን ማስፈረሙን አስታውቋል።

ዐመለ በክረምቱ አርባ ምንጭ ከተማን ለቆ ወደ መቐለ ከተማ ካመራ በኋላ ሙሉውን የውድድር ዓመት ከተለመደው የአጥቂ ስፍራ በተቃራኒ በተከላካይ አማካይነት ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን ጥሩ እንቅስቃሴም አሳይቷል። የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና አጥቂ በአዳማ ከተማ ለሁለት የውድድር ዓመት ለመጫወት ሲስማማ በቡድኑ በርካታ የአጥቂ አማራጮች በመኖራቸው በአማካይ ስፍራ ላይ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል። 

አዳማ ከዐመለ ቀደም ብሎ አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀም እና አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ የሚታወስ ነው።