13ኛው የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የታዳጊዎች ውድድር ተጠናቀቀ

በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አዘጋጅነት ለ13ኛ ጊዜ የተካሄደው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መታሰብያ ከ15 ዓመት በታች ታዳጊዎች ውድድር በዛሬው እለት ተጠናቋል።

በውድድሩ የመጨረሻ ቀን የዋንጫው ጨዋታ ከመደረጉ በፊት ለደርጃ  የአንለያይም ከ መካኒሳ ባደረጉት  ጨዋታ መካኒሳ 4-2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። 

በቀጣይ የፍፃሜ ጨዋታ አቶ አብነት ገብርመስቀል እና የዕለቱ የክብር ዕንግዶች ለሁለቱም ታዳጊ ቡድኖች ሰላምታ በመስጠት ያስጀመሩት ነበር። ጨዋታው በተጀመረ በ2ኛው ደቂቃ ግብ ማስቆጠር የቻለው  ቴውድሮስ ተካልኝ ከርቀት በመታው ኳስ የድል ቡድንን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል ። ከግቡ መቆጠር ባኋላ ወደፊትም በመጠጋት የታሻሉት የነበሩት ድሎች ነበሩ። በ30ኛው ደቂቃ ከነገው ተስፍ ቡድን አብዱል ያገኘው አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል። የአቻ ግብ ፍለጋ ተጭነው ለመጫወት የሙከሩት የነገው ተስፋዎች በበኩላቸው ሳይሳካላቸው የመጀመሪያው አጋማሽም ተጨማሪ ግብ ሳይታይበት ተጠናቋል።  

ከዕረፍት መልስ የድል ቡድን በ54ኛው ደቂቃ ኳስ ከሳጥን ውስጥ በእጅ በመነካቷ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ቴውድሮስ ተካልኝ  ወደ ግብነት በመለወጥ ልዩነቱን ወደ ሁለት ከፍ በማድረግ ችሏል። እስከ 70ኛው ደቂቃ የኳስ ብልጫ የወሰደው የድል ቡድን በቀሪዎቹ ደቂቃዋች የተስፋ ቡድን በማጥቃቱ መሻሉን ተከትሎ ወደ መከላከሉ አመዝኗል። ሆኖም በተጨማሪ ደቂቃ ዳንኤል ፍቃዱ ለድል ቡድን ተጨማሪ ግብ አስቆጥሩ ጨዋታው በድል ቡድን 3-0 አሸናፊነት ተጠናቆል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ ባኋላ የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ አብነት እንዲሁም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳዊት እና  ስራ አስኪያጁ አቶ ሰለሞን በሽልማት ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል። በክቡር አቶ ይደነቃቸው መታሰቢያ ውድድር ላይ 4ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው ቡድን አንለያይም የኳስ ሽልማት ሲያገኝ ከአንድ እስክ ሦስት ለወጡት ድል ፣ የነገው ተስፋ እና መካኒሳ ቡድኖች በየደረጃቸው ካገኟቸው ሜዳሊያዎች በተጨማሪ የትጥቅ እና የኳስ ሽልማቶችን አግኝተዋል። 

በተጨማሪም የውድድሩ ኮከብ ተጨዋች እዮኤል ፋሲል  ፣ በኮከብ ግብ አግቢነት ቅዱስ ግርማ ፣ በፀባይ ደግሞ  የኢትዮጵያዊ ቡድን ተሸላሚ ሆነዋል። በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ ለውድድሩ መሳካት የበኩላቸውን ትብብር ያደረጉ አካሎችም ከአቶ አብነት ገ/መስቀል ሽልማታቸውን ወስደዋል።