የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች 10 ቀን በኋላ መደረግ ይጀምራሉ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከባለፈው የውድድር ዓመት የተላለፉት የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎችን በዚህ ወር ያደርጋል። 

ውድድሩ ክፍት ቦታዎች በሚገኙበት ወቅት ሁሉ ሲደረግ ቆይቶ እስከ ሐምሌ 9 ድረስ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን አንድ የሩብ ፍፃሜ፣ ሁለት የግማሽ ፍፃሜ እና የፍፃሜ ጨዋታዎች ሳይከናወኑ ወደ 2011 መሸጋገራቸው የሚታወስ ነው። ፌዴሬሽኑ በወሰነው ውሳኔ መሠረት በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና መካከል የሚደረገው የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ መስከረም 12 ቀን 2010 ሲከናወን አሸናፊው ቡድንም መከላከያ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ጅማ አባ ጅፋርን በግማሽ ፍፃሜው ይቀላቀላል። የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎቹ መስከረም 15 ተካሂደው የፍፃሜ ጨዋታው እሁድ መስከረም 19 የሚከናወን ይሆናል። 

በተያያዘ ዜና ፌዴሬሽኑ ፕሪምየር ሊጉን ጥቅምት 17 እና 18 ለማከናወን የወሰነ ሲሆን በውድድሩ ዙርያ ከክለቦች ጋር ለመምከር እና የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱን ለማከናወን መስከረም 7 ሊሰበሰብ እንደሚችል ተነግሯል።