ፋሲል ከነማ ናይጄርያዊያን አጥቂዎች አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም ቀዳሚ የሆነው ፋሲል ከነማ ናይጄርያውያኑ አጥቂዎች ኢዙ ኢዙካ እና ኢፌኒ ኤዴን ማስፈረሙን በፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል። 
ኢፌኒ ኤዴ ወደ አጼዎቹ ቤት በዛሬው እለት ከፈረሙት መካከል ነው። በሀገሩ ክለቦች ኦሽን ቦይስ፣ ኢንየንባ እና ኢኑጉ ሬንጀርስ የተጫወተው የ27 ዓመቱ ኤዴ በ2016/17 ወደ አልባኒያው ኬኤፍ ቲራና ያመራ ሲሆን በ2014 የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒየንሺፕ (ቻን) የናይጄርያ ብሔራዊ ቡድን አባል ነበር።

ኢዙ አዙካ ሌላው የአጼዎቹ አዲስ ፈራሚ ነው። የ29 ዓመቱ ናይጄርያዊ አጥቂ ከ2008 ጀምሮ በሀገሩ ናይጄርያ፣ አልጄርያ፣ ቱኒዚያ፣ ካዛኪስታን፣ ቱርክ እና ሊቢያ በሚገኙ 13 ክለቦች ተዟዙሮ የተጫወተ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ህንዱ የሱፐር ሊግ ክለብ ጃምሸድፑር አምርቶ ከአንድ ዓመት በላይ ሳይቆይ ወደ ፋሲል አምርቷል። ለናይጄርያ ብሔራዊ ቡድንም ሶስት ጊዜ የመጫወት እድል አግኝቷል።

በክረምቱ 10 እና 11ኛ ተጫዋቾቻቸውን ያስፈረሙት አጼዎቹ በአጥቂ መስመር ላይ እምብዛም ተሳትፎ ሳያደርጉ ቆይተው የነበረ ቢሆንም በመጨሻዎቹ ሶስት ዝውውራቸው ፋሲል አስማማው ኢዙ አዙካ እና ኢፌኒ ኤዴን ማስፈረም ችለዋል።