ሴቶች ዝውውር | መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በሴቶች ፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮት ከአዳዳ ከተማ በመቀጠል በርካታ ተጫዋቾችን ያስፈረመው መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን በማስፈረም ወደ ቡድኑ የቀላቀላቸውን አዳዲስ ተጫዋቾች ቁጥር ስድስት አድርሷል።

በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ሲያሳዩ የቆዩት ሲሳይ ገብረወልድ እና አረጋሽ ከልሳ ወደ ጦሩ ያመሩ ተጫዋቾች ናቸው። ሁለቱ ተጫዋቾች በሴቶች ብሔራዊ ቡድን የተለያዩ የእድሜ እርከኖች አባል የነበሩ ሲሆን በተለይ ከኮፓ ኮካ ኮላ ውድድር የተገኘችው አረጋሽ ከልሳ በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከአልጄርያ ጋር በተደረገው ጨዋታ ከተመልካች አድናቆትን ያተረፈ እንቅስቃሴ አሳይታለች።

መከላከያ ከዚህ ቀደም መሰሉ አበራ፣ ገነት አክሊሉ፣ ፀሀይነሽ ዱላ እና ምህረት ኃይሉን ማስፈረሙ ይታወሳል።