ሴቶች ዝውውር | ጌዴኦ ዲላ ስድስት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወሳኝ ተጫዋቾቹን ያጣው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊው ጌዴኦ ዲላ ስድስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል። 

የሀዋሳ ከተማዋ አማካይ ትርሲት መገርሳ፣ በሲዳማ ቡና ያሳለፉት አጥቂዋ ረድዔት አስረሳኸኝ፣ ተከላካይዋ ማዕረግ ቴኮ እና አማካይዋ መሐሪ በቀለ፣ የአዳማ ከተማዋ አጥቂ ድንቅነሽ በቀለ፣ የፋሲል ከነማዋ የመስመር አጥቂ መንፈስ መቸነህ ወደ ጌዴኦ ዲላ ያመሩ ተጫዋቾች ናቸው።

ጌዴኦ ዲላ በዚህ ክረምት ሳራ ነብሶ እና ገነሜ ወርቁን የመሳሰሉ ቁልፍ ተጫዋቾችን ወደ አዳማ እና ንግድ ባንክ መሸኘቱ ይታወሳል።