ደቡብ ፖሊስ ሶስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጉን ካረጋገጠ በኋላ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ሦስት ተጫዋቾችን በማስፈረም ወደ ቡድኑ የቀላቀላቸውን አዳዲስ ተጫዋቾች ቁጥር አምስት አድርሷል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት መከላከያን ለቆ ወደ አውስኮድ አምርቶ የነበረውና በዓመቱ አጋማሽ ወደ መቐለ ከተማ ያቀናው አጥቂው ካርሎስ ዳምጠው ደቡብ ፖሊስን ተቀላቅሏል። በ2010 ወደ ድሬዳዋ ከተማ አምርቶ የነበረው የመስመር ተከላካዩ አናጋው ባደግ ሌላው ደቡብ ፖሊስን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው። መተሐራ ስኳርን ለቆ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ካመራ በኋላ ያለፉትነ ሁለት ዓመታት በክለቡ የቆየው የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዘሪሁን አንሼቦም ወደ ደቡብ ፖሊስ ያመራ ተጫዋች ነው። ሶስቱም ተጫዋቾች በአንድ ዓመት ውል ነው ክለቡን የተቀላቀሉት።

ከአዳዲስ ተጫዋቾች ጎን ለጎን የነባሮቹን ኮንትራት በማደስ ላይ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሐብታሙ ጥላሁንን ውል በተጨማሪ አንድ ዓመት አድሷል።