የሴቶች ዝውውር | አዲስ አበባ ከተማ 16 ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ረቡዕ መስከረም 09 2011

ህዳር 1 ለሚጀምረው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ በዘንድሮ አመት ከ2ኛ ዲቪዝዮን ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን ያደገው አዲስ አበባ ከተማ ለውጦችን እያደረገ ነው። ክለቡ በቅርቡ አሰልጣኝ መሰረት ማኔን በሁለት ዓመት ኳንትራት መቅጠሩም የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ በነባር ቡድኑ ውስጥ የሚገኙ 10 ተጨዋቾችን ውል ሲያድስ በርካታ አዳዲስ ተጨዋቾችንም ከአንደኛ ዲቪዚዮን እና ከሁለተኛ ዲቪዝዮን ከሚገኙ ክለቦች አምጥቷል።

በዚህም መሰረት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤዛዊት ተስፋዬ ፣ ቤተልሄም ሰማን ፣ ፍቅርተ ብርሃኑ እና እታፈራው አድርስን ፤ ከደደቢት ሰላም ላከ ፣ ቤዛ ታፈሰ ፣ ኤደን ሽፈራው እና ፍፁም ተስፋዬን ፤ ከአዳማ አስካለ ገብረፃዲቅ ፣ ሳሳሁልሽ ስዩም እና ገነት ፈረደን ፤ ከኢትዮጽያ ቡና ምንትዋብ ዮሐንስን ፣ ከኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ቅድስት ቦጋለን ፣ ከአካዳሚ ፎዚያ መሀመድን ፣ ከሻሸመኔ ሄለን መለሰን እንዲሁም ከልደታ ዘወትር ውርጋን አስፈርሟል።