ደደቢት የአንድ ተጫዋች ዝውውርን አጠናቋል

ለአዲሱ የውድድር ዓመት ቡድኑን በአዲስ መልክ በሊጉ ደረጃ ዝቅተኛ ክፍያ በሚከፈላቸው ተጫዋቾች እያዋቀረ የሚገኘው ደደቢት ያሬድ መሀመድን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። 

የመስመር ተጫዋቹ ያሬድ መሀመድ ከሀዋሳ ከተማ የ17 ዓመት በታች ቡድን በ2009 ወደ 20 ዓመት በታች ቡድን አድጎ ለሁለት የውድድር ዓመታት የቆየ ሲሆን በቡድኑ ያለውን ቆይታ አጠናቆ በሁለት ዓመታት ውል ደደቢትን ተቀላቅሏል። ሰማያዊዎቹ ከያሬድ በተጨማሪ ከጅማ አባ ቡና ጋር የነበረውን ውል ያጠናቀቀው ሌላው የመስመር አማካይ ኪዳኔ አሰፋን ለማስፈረም ተቃርቧል። በነገው ዕለትም ለክለቡ ፊርማውን እንደሚያኖር ይጠበቃል።

አመዛኞቹ ተጫዋቾቹን ወደ ሌሎች ክለቦች የሸኘው ደደቢት በዚህ የዝውውር መስኮት እስካሁን ሰባት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።