ሀዋሳ ከተማ ከአዲስ ፈራሚው ጋር ተለያየ

ሀዋሳ ከተማ ከሁለት ሳምንታት በፊት አስፈርሞት ከነበረው ቶጓዊው አጥቂ ክዎሚ ፎቪ አጉዊዲ ጋር መለያየቱ ታውቋል። 

አጥቂው በጳጉሜ ወር ወደ ክለቡ ከመጣ ጀምሮ የቅድመ ውድድር ዝግጅት አካል ሆኖ ልምምድ ሲሰራ የቆየ ቢሆንም ከሁለት ቀናት በፊት በተደረገለት ምርመራ ጉልበቱ ላይ ጉዳት ያለበት መሆኑ መረጋገጡ ከክለቡ ጋር እንዲለያይ ምክንያት ሆኗል። ሀዋሳ በአጉዊዲ ምትክ በአጥቂ ስፍራ ላይ ሌላ ተጫዋች ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ ሲሆን አይቮሪኮስታዊ ተጫዋችን ለሙከራ ወደ ሀገር ቤት እንዳስመጣ ተሰምቷል።