ሴቶች ዝውውር | አዳማ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾች ማስፈረሙን ቀጥሏል 

በዝውውር መስኮቱ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እየቀላቀለ የሚገኘው የአዳማ ከተማ ሴቶች ቡድን ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። 

ከክለቡ ጋር ስሟ ሲያያዝ የቆየችው እፀገነት ብዙነህ ፊርማዋን አኑራለች። የቀድሞዋ የንግድ ባንክ ተጫዋች የ2010 የውድድር ዓመትን ያሳለፈችው በደደቢት ነበር። በኤሌክትሪክ ደካማ የውድድር ዓመት መልካም ጊዜ በማሳለፍ ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች መካከል አንዷ የሆነችው የአጥቂ መስመር ተሰላፊዋ ጤናዬ ወመሴ ሌላዋ ፈራሚ ናት።

እስካሁን በዝውውር ገበያው አስር ተጫዋቾችን አስፈርሞ የወሳኘረ ተጫዋቾቹን ውል ያደሰው አዳማ ከተማ ህዳር 1 ለሚጀመረው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ቅድመ ውድድር ዝግጅቱን መስከረም 20 እንደሚጀምር ታውቋል።