ጅማ አባ ጅፋር በውሳኔው ፀንቷል 

የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሸ ፍፃሜ ጨዋታውን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለማድረግ መርሐ ግብር ወጥቶለት የነበረው ጅማ አባ ጅፋር ለውድድሩ ዝግጅት እንዳላደረገ በመግለፅ እንደማይጫወት ማሳወቁ የሚታወስ ነው።

ከጅማ አባ ጅፋር ውሳኔ በኋላ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታውን እንዲያደርግ በደብዳቤ ማሳሰቡን ተከትሎ ቡድኑ ወደ ሀዋሳ ጉዞ ሊያደርግ ይችል ይሆን የሚል ጥያቄዎች ቢኖሩም ምሽቱን በተደረገ ስብሰባ ወደ ሀዋሳ ላለመጓዝ በወሰነው ውሳኔ መፅናቱ ታውቋል። በነገው ዕለት ጠዋትም የቅድመ ውድድር ዝግጅት እያደረገ በሚገኝበት አዳማ መደበኛ ልምምዱን ማከናወን እንደሚቀጥል ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከጅማ አባ ጅፋር ጋር በተያያዘ ዜና በክረምቱ ያስፈረማቸው አሉላ ግርማ (ጉዳት) እና ሲሳይ ቶሊ (አቋም) ከክለቡ ጋር መለያየታቸውን ክለቡ አስታውቋል።