ድሬዳዋ ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

በዝውውር ገበያው ተሳትፎውን የቀጠለው ድሬዳዋ ከተማ በክረምቱ ሁለተኛ ግብ ጠባቂ በማስፈረም ምንተስኖት የግሌን በእጁ አስገብቷል። 

ምንተስኖት ወደ ደደቢት ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ በተጠባባቂ ግብ ጠባቂነት ሲጫወት የቆየ ሲሆን ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት ብሔራዊ ቡድንም አገልግሏል። በሁለት ዓመት ኮንትራት ድሬዳዋን የተቀላቀለው ወጣቱ ግብ ጠባቂ ምንተስኖት በክለቡ ከዚህ ቀደም በደደቢት ካሰለጠኑት ዮሀንስ ሳህሌ ጋር በድጋሚ ሲገናኝ ለመጀመርያ ተሰላፊነት ከሳምሶን አሰፋ እና ሌላው የክረምት ፈራሚ ፍሬው ጌታሁን ጋር መፎካከር ይጠበቅበታል።

ድሬዳዋ ከተማ እስካሁን 11 አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በመቐለ እያከናወነ ይገኛል።