ዮናታን ከበደ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አመራ

ድሬዳዋ ከተማ የመስመር አጥቂው ዮናታን ከበደን አስፈርሟል ፡፡

ከሀዋሳ ከተማ የተገኘው የመስመር እና የፊት አጥቂው ዮናታን ከበደ በ2009 ወደ ቀድሞ ክለቡ ሀዋሳ ቢመለስም በጉዳት እምዛም የመሰለፍ እድልን ማግኘት ሳይችል በ2010 የውድድር ዘመን በሁለት ክለቦች ውስጥ ለማሳለፍ ተገዷል። ወደ አርባምንጭ ከተማ በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም አማካኝነት ቢያመራም የተጠበቀውን ያህል መሆን ሳይችል ወደ ወላይታ ድቻ በመጋቢት ወር አምርቶ የ6 ወራት ቆይታን ካደረገ በኃላ ከክለቡ ጋር ቀሪ የስድስት ወራት ኮንትራት እየቀረው በመለያየት ወደ ድሬዳዋ ከተማ በአንድ ዓመት ውል አምርቷል፡፡ 

ከ36 በላይ የሙከራ ዕድል እየሰጠ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ዮናታን ከበደንም በሙከራ ባሳለፈው ጊዜ እንዳስፈረመው ሰምተናል።