“ከኢትዮጵያ ጋር እንደምንፎካከር አስባለሁ ” የኬንያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሴባስቲያን ሚኜ

ነገ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጠመው የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሴባስቲያን ሜኜ ስለ ጨዋታው እና ስላደረጉት ዝግጅት ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታን አድርገዋል፡፡ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

” ዝግጅታችን ከባድ ነበር። ምክንያቱም ሁሉንም ተጨዋቾቼን ያገኘኋቸው ገና ሰኞ ነው፡፡ ይህም ማለት ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ ለመሆን ያለን ሁለት ቀን ብቻ ነው፡፡ ይህ የእግርኳስ አንዱ አካል ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር እንደምንፎካከር አስባለው፡፡


” ከጋና ጋር በጣም ጥሩ ውጤት ነበር ያስመዘገብነው፤ ግን ከባዱ ነገር ይሄንን እንቅስቃሴ ደግሞ ማሳየት ላይ ነው፤ ይሄ ነው የእኛ ፈተና፡፡ እናውቃለን እዚህ ያለው ጨዋታ እንደሚከብደን፡፡ በአጫጭር ቅብብል መጫወት የሚችል እና ከኬንያ በተሻለ በቅርቡ ለአፍሪካ ዋንጫ መብቃታችሁን አውቃለው፡፡ ግን ተፎካከረን ለኬንያ እግርኳስ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ተዘጋጅተናል፡፡ አሁን ገና መጀመራችን ነው፡፡
“ስለተጋጣሚ ቡድኖች ማወቅ ስራዬ ነው፡፡ አዲስ አሰልጣኝ እንዳላችሁ አውቃለው፡፡ ጥሩ ስራዎችን እንደሰራም አውቃለው፡፡ ለእኛ ጥሩ ፈተና ነው ብዬ ነው የምጠብቀው፡፡”