የቡድን ዜና | ኬንያን የሚገጥመው የዋልያዎቹ የመጀመርያ አሰላለፍ ታውቋል 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው እለት ሶስተኛ የምድብ ማጣርያ ጨዋታውን ከኬንያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም ያደርጋል። 

በ2011 የመጀመርያ የነጥብ ጨዋታውን የሚያደርገው ብሔራዊ ቡድኑ ለኬንያው ጨዋታ የመጀመርያ 11 ተጫዋቾችን ለይቷል። 

 ቡድነ ጳጉሜ አራት ከሴራሊዮን ጋር ከተደረገው ጨዋታ የአንድ ተጫዋች ብቻ ለውጥ ያደረገ ሲሆን ዳዋ ሆቴሳ የመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ ተካቶ ኡመድ ተጠባባቂ ሆኗል።

የመጀመርያ አሰላለፉ ይህንን ይመስላል:- 

(4-2-3-1)

ሳምሶን አሰፋ

አብዱልከሪም መሐመድ – አስቻለው ታመነ – አንተነህ ተስፋዬ –  አህመድ ረሺድ

ጋቶች ፓኖም – ሙሉዓለም መስፍን 

ቢንያም በላይ – ሸመልስ በቀለ – ዳዋ ሆቴሳ

ጌታነህ ከበደ (አ)

– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካልሲ የሚያደርግ ሲሆን ጨዋታው በሱፐር ስፖርት 9 ኢስት ላይ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል። ኢቲቪም ለሀገር ውስጥ ተመልካቾች ጨዋታውን ለማስተላለፍ በጥረት ላይ መሆኑን ሰምተናል።