ጅማ አባ ጅፋር እና ይስሀቅ መኩርያ ተለያይተዋል

ጅማ አባ ጅፋር ከአዳዲስ ፈራሚዎቹ መካከል አንዱ የሆነው ይስሀቅ መኩሪያን ውል አቋርጧል።

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ጅማ አባ ጅፋርን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል ይስሀቅ ይስሀቅ መኩርያ አንዱ ነው።
ይስሀቅ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ በአማካይ ተከላካይነት እና በመሀል አማካይነት ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን
ጅማ አባ ጅፋር በክረምቱ የዝውውር መስኮት የአማካይ ስፍራ ተጫዋቾቹ መልቀቃቸውን ተከትሎ ያለበትን ክፍተት ይሸፍናል ብሎ በማመን አስፈርሞት ነበር።

ሆኖም ከክለቡ አመራሮች እንዳገኘነው መረጃ በቅድመ ውድድር ዝግጅት በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የተጨዋቹ አቋም እንደተጠበቀው ሆኖ ባለመገኘቱ ውሉ እንደተቋረጠ ሰምተናል። በሌላ በኩል ተጨዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት በክለቡ አመራሮች የተሰጠው አስተያየት ተገቢ እንዳልሆነ የተናገረ ሲሆን ከቡድኑ የተቀነሰውም እግር ኳሳዊ ባልሆነ ምክንያት መሆኑን እንደሚያምን ተናግሯል።