ደቡብ ፖሊስ ዳዊት አሰፋን አስፈረመ

የከፍተኛ ሊግ ቻምፒዮን በመሆን ወደ ፕሪምየር ሊግ ያደገው ደቡብ ፖሊስ ዳዊት አሰፋን አስፈርሟል፡፡

ግብ ጠባቂው ባሳለፍነው ዓመት በጅማ አባ ጅፋር ያሳለፈ ሲሆን ጋናዊው የመጀመርያ ተመራጭ ግብ ጠባቂ ዳንኤል አጄይ በግል ጉዳይ ከክለቡ ርቆ በቆየባቸው ጥቂት ጊዜያት ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ከቡድኑ ጋርም የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አሳክቶ በክረምቱ በመለያየት አዲስ አዳጊው ደቡብ ፖሊስን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሏል፡፡

ዳዊት በሚሌንየሙ መጀመርያ በሐረር ቢራ ቆይታው በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ ብቅ ካሉ ተስፈኛ ግብ ጠባቂዎች አንዱ የነበረ ቢሆንም የሚጠበቀውን ያል እድገት ሳያሳይ ቀርቷል፡፡ ከሐረር በኋላም በመከላከያ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም ጅማ አባጅፋር አሳልፏል፡፡