የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፍፃሜ ቀን ተለውጧል

ትናንት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች የተከናወነበት የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመዝጊያ ቀን ተቀይሯል።

የ13ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር የደረጃ እና የፍፃሜ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ዕለት ዕሁድ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ክለቦች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በድጋሜ የቀን ለውጥ ተደርጎበታል። በዚህም መሠረት ሁለቱም ጨዋታዎች ቅዳሜ ጥቅምት 10 ቀን የሚደረጉ ሲሆን ቀደም ብሎም በ8፡00 ሰዓት የሰናይ መስማት የተሳናቸው እግር ኳስ ክለብ እና የአርቲስቶች የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ።

እንደወጣው የመጨረሻ መርሀ ግብርም ቅዳሜ በ09፡00 መከላከያ ከጅማ አባ ጅፋር ለሦስተኝነት ሲጫወቱ 11፡00 ላይ ደግሞ ባህር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ለፍፃሜ እንደሚፋለሙ ተረጋግጧል።