ከፍተኛ ሊግ: አዲስ አበባ ከተማ 13 አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

የከፍተኛ ሊግ ክለብ የሆነው አዲስ አበባ ከተማ የአሰልጣኝ ቅጥር በመፈጸም ለ2011 የውድድር ዘመን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ 13 አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የዘጠኝ ነባር ተጫዋቾችንም ውል ማድሱ ታውቋል፡፡  

መስከረም ወር ላይ በወደ ፕሪምየር ሊግ ቡድኖችን በማሳለፍ ልምድ ያለቸው ሰልጣኝ መኮንን ገብረዮሀንስን የሾመው አዲስ አበባ ከተማ በፕሪምየር ሊጉ ረጅም ዓመታት የተጫወቱ እና በከፍተኛ ሊጉ ጥሩ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጫዋቾችን ነው ወደ ቡድኑ የቀላቀለው፡፡

አዲስ ፈራሚዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

ቢንያም ሐብታሙ (ከፋሲል/ግብ ጠባቂ)፣ ከድር ሳሊህ (ከወልዋሎ/አጥቂ)፣ የተሻ ግዛው (ከመከላከያ/ አጥቂ)፣ ኢብሳ በፍቃዱ (ከሀድያ ሆሳዕና/ አጥቂ)፣ በረከት ከማል (ከደሴ / አጥቂ)፣ ዓለማየሁ ሙለታ ( ከኢት. ቡና/ ተከላከይ)፣ በቃሉ ገነነ (ከአውስኮድ/ አማካይ)፣ ሙሉጌታ አሰፋ (ከአውስኮድ/ግብጠባቂ)፣ አስራት ሸገሬ (ከወሎ ኮምበልቻ/ አማካይ)፣ አብርሃም (ከሰበታ/ተከላካይ)፣ ቀፀላ ፍቅረማርያም (ከአውስኮድ/ አጥቂ)፣ ኤርሚያስ ፍሰሃ (ከአውስኮድ/አጥቂ) እና በድሩ ኑርሁሴን (ከአውስኮድ/አጥቂ)

ከአዲሶቹ በተጨማሪ የዘጠኝ ተጫዋቾችን ውል ያደሰው አዲስ አበባ ከተማ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ዝግጅቱን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እያደረገ ይገኛል። ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት መኮንን ገብረዮሀንስ፣ በምክትል አሰልጣኝነት ለኢትዮጽያ ቡና ምክትልነት ታጭተው የነበሩት እስማኤል አቡበከር፣ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ መሠረት ወልደማርያም፣ ቡድን መሪ ፍሬይሁን ወልዴ እንዲሁም ቴክኒክ ዳይሬክተር ዳንኤል ገብረማርያም ይመሩታል።