ሽረ እንዳሥላሴ ዓብዱሰላም አማንን አስፈረመ

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደጋቸው ካረጋገጡ በኋላ በዝውውር መስኮቱ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ሽረ እንዳሥላሴዎች ዓብዱልሰላም አማንን አስፈርመዋል።

በ2009 ወልዋሎ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያልፍ ካስቻሉት ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ይህ የመስመር ተከላካይ ያለፈው ዓመት መጀመርያ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ቢዘዋወርም በክለቡ ስኬታማ ጊዜ ባለማሳለፉ ውሉ ሳይጠናቀቅ በመለያየት በውድድር ዘመኑ አጋማሽ የዝውውር መስኮት የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ወሎ ኮምቦልቻን ተቀላቅሎ እስከ ዓመቱ ፍፃሜ ከ ክለቡ ጋር ቆይቶ ነበር።

ዓብዱሰላምን ጨምሮ ስምንት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ሽረዎች በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ተጫዋቾች ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።