መሐመድ ናስር ማረፊያው ሲዳማ ቡና ሆኗል

ሲዳማ ቡና በአዲስ ግደይ ላይ ጥገኛ የሆነው የማጥቃት አቅሙን እንዲያግዝ መሐመድ ናስርን አስፈርሟል።

ያለፉትን ሁለት ዓመታት የፊት መስመሩን ለማጠናከር በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ተጨዋቾች ቦታውን ለመሸፈን ጥረት ቢያደርግም ከአዲስ ግደይ ውጭ ሁነኛ የፊት መስመር አጥቂ ማግኘት እየተቸገረ የሚገኘው ሲዳማ ቡና የአጥቂ ክፍተቱን ለመቅረፍ በማሰብ በፕሪምየር ሊጉ በበርካታ ክለቦች በመጫወት ልምድ ያለውን መሐመድ ናስርን ለአንድ ዓመት ኮንትራት አስፈርሟል።

መሐመድ ናስር ያለፉትን 12 ዓመታት በጅማ ከተማ ፣ መከላከያ ፣ ኒያላ ፣ ኢትዮ ኤሌትሪክ ፣ አዳማ ከተማ ፣ ኢትዮዽያ መድን ፣ ኢትዮዽያ ቡና ፣ በሱዳኑ አሃሊ ሸንዲ እና ጅማ አባቡና መጫወት የቻለ ስኬታማ ተጫዋች ነው። 2010 የውድድር ዘመን ዘግይቶም ቢሆን ፋሲል ከነማን የተቀላቀለው መሐመድ አመዛኙን ጨዋታ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ሆኖ ቢያሳልፍም ወደ መጀመርያ ተሰላፊነት በተመለሰበት አጋጣሚ ሁለት ተከታታይ ጨዋታ ላይ ጎል ማስቆጠር ቢችልም ከአፄዎቹ ጋር የሚያቆየው ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት እየቀረው በስምምነት መለያየቱ ይታወሳል።