የቅዱስ ጊዮርጊስ በሴቶች ቡድን ተሳታፊነቱ ይዘልቃል

በዘንድሮው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የመቀጠሉ እጣ ፈንታ ጥያቄ ውስጥ ገብቶ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ተሳታፊነቱን ለማስቀጥል የክለቡ ቦርድ ውሳኔ ማስተላለፉ ታውቋል፡፡
በዘንድሮው የዝውውር መስኮት አንድም ተጫዋቸ ማስፈረም ያልቻለው ክለቡ በረከት ያሉ ተጫዋቾች በመልቀቅ ወደ ሌላ ክለብ በማምራታቸው ምክንያት ክለቡ እንደሚፈርስ እና በሊጉ እንደማይሳተፉ የተነገረ ቢሆንም የክለቡ ቦርድ ትላንት ምሽት ባደረገው ስብሰባ ቡድኑ እንደሚቀጥል እና በሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደሚሳተፍ ከውሳኔ ላይ በመድረሱ በሊጉ ዳግም እንደምንመለከተው ተገልጿል፡፡ ሊጉ ሊጀመር ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ በቀረበት በአሁኑ ወቅት ተጫዋቾችን የማግኘት ዕድሉ ጠባብ በመሆኑ በሙከራ በመመልከት ለመቀላቀል መታሰቡን የክለቡ አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግራለች “አሁን ላይ ምንም ማድረግ አይቻልም፤ እንደ ቡድን መቀጠሉ በራሱ ጥሩ ነው። ያሰብኳቸውን ተጫዋቾች ማግኘት ስለማልችል ለማድረግ ያሰብኩት ለበርካቶች የሙከራ ጊዜን ሰጥቼ መሰብሰብ ነው። ያን ካደረኩ በኃላ ባለኝ ጊዜ ዝግጅት ጀምራለው ስትል።” ተናግራለች ፡፡

ክለቡ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በቢሾፍቱ የቅድመ ውድድር ዝግጅት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡