ከፍተኛ ሊግ | ቤንች ማጂ ቡና አስራ ሶስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ወደ ከፍተኛ ሊግ ባደገበት ዓመት ተፎካካሪ መሆን የቻለው ቤንች ማጂ ቡና አስራ ሶስት አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋችን ውል አራዝሟል፡፡

ሚዛን አማን በሚል ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ይጠራ የነበረውና በ2010 ስሙን ቤንች ማጂ ቡና በማለት የለወጠው ክለቡ ምንም እንኳን በመጀመሪያው አመት የከፍተኛ ሊግ ተሳትፎው ወጣ ገባ አቋምን ቢያሳይም ለተጋጣሚዎቹ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆኑን ያሳየ ክለብ ነበር። በዘንድሮው የውድድር ዘመን በውል ማለቅ ምክንያት ከአስር ተጫዋቾች ጋር የተለያየው ክለቡ ከአስራ ሁለት ነባር ተጫዋቾች ጋር ሲቀጥል አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ አምጥቷል። በዚህም መሠረት ግርማ ዓለሙ (ልደታ/አማካይ)፣ ቶማስ ዘገየ (ሞጆ ከተማ/ግብ ጠባቂ)፣ ቱፋ ተሺታ (ሞጆ/ተከላካይ)፣ ፍቃዱ ባርባ (ሞጆ/አማካይ)፣ ኃይለየሱስ ኃይሉ (ለገጣፎ/አማካይ) ቱሳ ሳዴቦ (አጥቂ/ደደቢት)፣ ሐብታሙ ሸንዴ (ሻሸመኔ/ተከላካይ)፣ ሊሌሳ ኤዲሳ (ግብ ጠባቂ/ነቀምት)፣ ምናሉ አበራ (ተከላካይ/አሶሳ)፣ ከማል አቶም (አጥቂ/አሶሳ)፣ መስፍን ጎሳዬ (ፌዴራል ፖሊስ/ተከላካይ)፣ ሰመረዲን እስማኤል (ቦንጋ/ተከላካይ)፣ አዲሱ ያሉባብ (ጅማ አባቡና/አማካይ) አዳዲስ ፈራሚ ሆነው ክለቡን የተቀላቀሉ ናቸው።

ክለቡ ከአዳዲስ ተጫዋቾች ፊርማ በተጨማሪ በዋና አሰልጣኝነት ወንዳየሁ ኪዳኔን (ፎቶ-ቀኝ) ይዞ ሲቀጥል አበራ ገብሬን (ፎቶ-ግራ) ምክትል አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል። ባሳለፍነው ዓመት ክለቡን የተቀላቀለው ኤሪክ ኮልማንን ውልም በአንድ ተጨማሪ ዓመት ማራዘሙን የክለቡ አሰልጣኝ ወንዳየው ኪዳኔ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አሰልጣኙ ባሳለፍነው ሳምንት ዝግጅት እንደጀመሩ ገልፀው በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ለመቀላቀል ማሰባቸውንም ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።