ከፍተኛ ሊግ| ካፋ ቡና ዋና እና ምክትል አሰልጣኞችን ቀጠረ

2010 የውድድር ዓመት በምድብ ለ ተመድቦ ውድድሩን ያከናወነው ካፋ ቡና ከዋና አሰልጣኙ ሰብስቤ ይባስ ጋር መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን በምትኩ ጳውሎስ ፀጋዬን ዋና አሰልጣኝ እንዲሁም መርሻ ሚደቅፃን ምክትል አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ1984-86 መጫወት የቻሉት አሰልጣኝ ጳውሎስ በአሰልጣኝነት ደብረ ብርሃን ከተማን ለሁለት ዓመታት፣ ቡራዩ ከተማን ለአራት ዓመታት፣ ጥቁር አባይን እንዲሁም አርባምንጭ ከተማን በከፍተኛ ሊግ እና ፕሪምየር ሊግ አሰልጥነዋል። አሰልጣኙ በአርባምንጭ ከተማ በ2009 ከተለያዩ በኋላ ያለ ክለብ ቆይተዋል።

በኢትዮጽያ እግር ኳስ ረዘም ያለ ጊዜ የቆዩት አሰልጣኝ መርሻ ሚደቅሳ በኢትዮጵያ ቡና፣ ንግድ ባንክ፣ ወንጂ፣ ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም በየመን የማስልጠን ልምድ ያላቸው አቶ መርሻ በአንድ ዓመት ውል የከፋ ቡና ምክትል አሰልጣኝ ሆነው የሚሰሩ ይሆናል።

አሰልጣኝ ጳውሎስ ፀጋዬ እና ምክትላቸው ከካፋ ቡና ጋር ጥቅምት አጋማሽ ላይ ዝግጅት የጀመሩ ሲሆን እስካሁን ስድስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል። አስራት ሚሻሞ (ግብ ጠባቂ/ሆሳዕና)፣ አብነት አባተ (ተከላካይ/ ሆሳዕና)፣ አሸናፊ ካሳ (አማካይ/የካ ክፍለ ከተማ)፣ ሙሉቀን ተስፋዬ (አማካይ/ሆሳዕና)፣ አድማሱ ጌትነት (አጥቂ/ሱልልታ)፣ አሸናፊ ከማል (ተከላካይ/ሱሉልታ) በአንድ ዓመት ውል ክለቡን ሲቀላቀሉ ሰባት ነባር ተጫዋቾች ውል አድሰዋል።