ከፍተኛ ሊግ | ቡራዩ ከተማ ዘጠኝ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በ2010 ውድድር ዓመት ጥሩ አጀማመር በማድረግ የምድቡ መሪ መሆን ችሎ የነበረውና በቀሪው የውድድር ዘመን ወጣ ገባ አቋም በማሳየት በሰንጠረዡ ወገብ ተቀምጦ ያጠናቀቀው ቡራዩ ከተማ ለ2011 የውድድር ዘመን ዝግጅቱን ከጥቅምት 10 ጀምሮ እያከናወነ ይገኛል። ክለቡ የዋና አሰልጣኙን አብዲ ቡሊ እና የምክትል አሰልጣኙ አጥናፉ ዓለሙን ውል ለአንድ ዓመት ያራዘመ ሲሆን 12 ተጫዋቾችን ውል ሲያድስ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ቀላቅሏል።

ቡራዩ ከተማ የተቀላቀሉ ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-
ጌቱ ተስፋዬ (ግብጠባቂ/ስልጤ ወራቤ)፣ ዳንኤል መስፍን (ግብ ጠባቂ/የካ ክፍለ ከተማ)፣ አሸናፊ ባልቻ (ተከላካይ/ካፋ ቡና)፣ ኤልያስ መንግስቱ (አማካይ/ዲላ)፣ ክንዳለም ፍቃዱ (አማካይ/ሰበታ)፣ ጫላ ከበደ (አማካይ/ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ)፣ ዳንኤል ለታ (አማካይ/አውስኮድ)፣ ማቲያስ ሹመት (ቤንጅ ማጂ ቡና) እና ፀጋዬ ከፍያለው (አጥቂ/አዲስ ከተማ)

በአዲሱ የከፍተኛ ሊግ ፎርማት መሰረት በምድብ ሀ (ማዕከላዊ ምድብ) የተደለደለው ቡራዩ ከተማ በመጀመርያው ሳምንት ከደሴ ከተማ ጋር ይጫወታል።