የአሰልጣኞች አስተያየት | ስሑል ሽረ 0-0 አዳማ ከተማ

ዛሬ ከተካሄዱት የሦስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች አንዱ የሆነው የስሑል ሽረ እና አዳማ ከተማ ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። 

“የዛሬ ጨዋታችን አቅደን እንደገባነው አይነት አልነበረም”ዳንኤል ፀሃዬ – ስሑል ሽረ  

የዛሬ ጨዋታችን አቅደን እንደገባነው አልነበረም። በመሃል ክፍል ላይ ተበልጠናል፤ ያ በመሆኑም ኳስን ተቆጣጥረን ለመጫወት ተቸግረናል። እነሱ ረጃጅም ኳሶችን በመጠቀም ተከላካይ ክፍላችንን ሲያስጨንቁ ተመልክቻለሁ። በአካል ብቃትም እነሱ ከኛ የተሻሉ ነበሩ። አቅደን የገባነውን የጨወታ ስልት ባለመተግበራችን ነጥብ ልንጥል ችለናል። ውጤቱ ለኛ ጥሩ አልነበረም። ቡድናችን አዲስ አዳጊ እንደመሆኑ ከጨዋታ ጨዋታ እንደሚሻሻል ነው የምጠብቀው። በቀጣይ ሳምንት ጨዋታዎች ተሻሽለን እንቀርባለን።

“የተፈጠረውን እድል መጠቀም ሳንችል ቀርተናል” ሲሳይ አብርሃም – አዳማ ከተማ 

የተሻለ ተጫውተን የጎል ኣጋጣሚዎች ፈጥረናል። በሁለቱም የጨዋታ ምዕራፎች ቢሆንም ልጆቼ ይቸኩሉ ስለነበር የተፈጠረውን አጋጣሚ መጠቀም ሳንችል ቀርተናል። በአጠቃላይ ዛሬ የአጨራረስ ችግር ነበረብን። ገና የጨዋታዎች ጅማሮ ስለሆነ በስራ የሚፈቱ ስለሆኑ አስተካክሎ መቅረብ ያለብን ዋነኛው ስራችን ይሆናል። ትምህርት የሰጠን ጨዋታ ነበር።