ቻምፒየንስ ሊግ | የጅማ አባጅፋር አሰላለፍ ታውቋል

የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የ2018/19 ቅድመ ማጣርያ ጨዋታውን ከጅቡቲው ቴሌኮም ጋር የሚያደርገው ጅማ አባ ጅፋር የመጀመርያ 11 ተሰላፊዎች ታውቀዋል። የቡድኑ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ከጉዳቱ ማገገሙ ቢነገርም በተጠባባቂነት የተያዘ ሲሆን አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የማጥቃት ባህርይ ያላቸው ተጫዋቾችን የያዘ አሰላለፍን ተጠቅመዋል።


የዛሬው አሰላለፍ የሚከተለው ነው:-

ዘሪሁን ታደለ

ዐወት ገ/ሚካኤል – አዳማ ሲሶኮ (አ) – ከድር ኸይረዲን – ኤልያስ አታሮ

ይሁን እንደሻው – ኤልያስ ማሞ – መስዑድ መሐመድ

አስቻለው ግርማ – ማማዱ ሴዲቤ – ዲዲዬ ለብሪ

ተጠባባቂዎች

ዳንኤል አጄይ፣ መላኩ ወልዴ፣ ተስፋዬ መላኩ፣ ያሬድ ዘውድነህ፣ ንጋቱ ገ/ሥላሴ፣ ኄኖክ ገምቴሳ፣ ኤርሚያስ ኃይሉ

12:00 የሚካሄደውን ጨዋታ ኤርትራዊያን ዳኞች እንደሚዳኙት ታውቀል።