ከፍተኛ ሊግ | ጅማ አባ ቡና ከግማሽ በላይ ስብስቡን በአዲስ ተክቷል

ጅማ አባቡና የሁለት የነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያድስ አስራ ስድስት የአዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል፡፡

በ2010 ከፍተኛ ሊግ በምድብ ለ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው ጅማ አባቡና በዘንድሮው ከፍተኛ ሊግ አዲስ አደረጃጀት በማዕከላዊ ደቡብ ምዕራብ ምድብ እደተደለደለ የሚታወስ ነው። ባሳለፍነው ሳምንት የተሰበሰበው የጅማ አባቡና ጠቅላላ ጉባኤ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በቡድኑ ላይ ተጋርጦ በነበረው የፍይናንስ ና አስተዳደራዊ ችግሮችን መፍትሔ በመስጠት ቡድኑን አደረጃጀት በመቀየር እና አዳዲስ አመራሮችን ወደ ቡድኑን በማምጣት መኮንን ማሞን ዋና አሰልጣኝ ፣ የታዳጊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ለማ ተሾመን በረዳትነት፣ ሐብታሙ በቀለን በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት በመሾም በጥቅምት ወር አጋማሽ ቢጀምሩም ነባር የቡድኑ ተጫዋቾች በኮንትራት መጠናቀቅ ምክንያት ያጧቸውን የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች ጨምሮ በሽያጭ ለአዳማ ከተማ አሳልፈው የሰጧውን ብዙዓየሁ እንደሻው እና ሱራፌል ጌታቸውን መተካት የአሰልጣኝ መኮንን ማሞ እና ረዳቶቻቸው የቤት ስራ ነበር ።

ውላቸውን ለአንድ ዓመት ያደሱ ነባር ተጫዋቾች: ሙላት አለማየሁ (ግብጠባቂ)፣ በኃይሉ በለጠ (የመሀል ተከላካይ)

ኮንትራት ያላቸው: አብዱል ቃድር ዘይኑዲን (አማካይ) ፣ ሮባ ወርቁ (አማካይ)፣ ወንድማገኝ ማርቆስ (የመስመር ተከላካይ)፣ አማኑኤል ጌታቸው (የመስመር ተከላካይ)፣ ካሚል ረሺድ (አማካይ)

አዲስ ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉ

ግብ ጠባቂ፡ ገመቹ በቀለ (ከአክሱም ከተማ)

ተከላካይ፡ አስቻለው ዘውዴ (ደሴ ከተማ)፣ ሮቤል ግርማ (ወልዋሎ ዓ.ዩ)፣ ኄኖክ ገታ (የካ ክ/ከተማ)፣ ዳዊት ታደሰ (ቡራዩ ከተማ)፣ ሣሙኤል አሸብር (ስልጤ ወራቤ)፣ ዳንኤል ራህመቶ (ኤሌክትሪክ)

አማካዮች፡ አብዱልአዚዝ ሚፍታህ (ኢኮስኮ)፣ አብዱልከሪም አባፎጊ (ቤንችማጂ ቡና)፣ ፓጋንግ ተቺዎ (ስሑል ሽረ)፣ አቤል አንበሴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

አጥቂዎች፡ ካርሎስ ዳምጠው (አማራ ውሃ ስራ)፣ ጃፈር ከበደ (ቤንች ማጂቡና)፣ ሣፎ ቁሪ (ነጌሌ ከተማ)፣ ፉዐድ ተማም (ሀላባ ከተማ)፣ ሊቁ አልታየ (ፌደራል ፖሊስ)


የቡድኑ አሰልጣኝ መኮንን ማሞ መጀመርያ በወጣው የከፍተኛ ሊግ መርሀ ግብር መሰረት ውድድሩ ሊጀመር ሃያ ቀናት ብቻ ሲቀሩት ወደ ቡድኑ ቢቀላቀሉም አሁን ያሰባሰቧቸውን ተጫዋቾች ጠንካራና ተፎካካሪ ለመሆን እንዳቀዱ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በወዳጅነት ጨዋታ ወደ ሰበታ በማቅናት 3-2 ቢሸነፉም አዲሱ ስብስብ ላይ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እንዳዩ ገልጸው አሁንም ክፍተቶች ባዩባቸው የአማካይ እና የአጥቂ ስፍራ ላይ ሁለት ወይም ሶስት ተጫዋቾችን ሊያካትቱ እንደሚችሉም አክለዋል።

ጅማ አባ ቡና ከነጌሌ አርሲ ጋር የሚያደርገው የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታ የተጫዋቾቹን ምዝገባ ዘግይቶ በማከናወኑ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል።

.