የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የባህር ዳር ከተማን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል

በአምስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መቐለ ላይ መቐሌ 70 እንደርታ ባህር ዳር ከተማን እንዲያስተናግድ ቀደም ብሎ መርሃ ግብር መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ተጋባዦቹ ባህር ዳር ከተማዎች ከቀናት በፊት ለፌደሬሽኑ በላኩት ደብዳቤ ዝርዝር ጉዳዮችን አስረድተው ጨዋታው እንዲራዘምላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል። 

የባህር ዳር ደብዳቤ 

በትግራይ እና በአማራ ክለቦች መካከል በሁሉም የሊግ እርከኖች በተደረጉ የእርስ በእርስ ጨዋታዎች በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወቱ ሲደረግ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከኢትዮጵያ ባህል እና ቱሪዝማ ሚ/ር ድኤታ እና ከኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋር በመተባበር የሁለቱ ክልል መስተዳድሮችን በማናገር ጨዋታዎች በሰላማዊ መልኩ በየራሳቸው ሜዳ  እንዲከናወኑ መወሰኑ ይታወሳል። ቢሆንም ግን ባህር ዳር ከተማ ከሁለት ቀናት በፊት በላከው ደብዳቤ”በቅድሚያ ባህር ዳር ላይ በሶስተኛ ሳምንት ከስሑል ሽረ ጋር የማደርገው ጨዋታ ይከናወን፤ ኃላፊነት የሚወስድ አካል ባለመኖሩ የደህንነት ስጋት አለብኝ” በማለት ጨዋታው እንዲራዘምለት ጠይቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሊግ ኮሚቴም የክለቡን ጥያቄ ተመልክቶ ጨዋታው በተያዘለት ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ እንደሚደረግ ለውጥም እንደማይኖር ለክለቡ በላከው ደብዳቤ አስረድቷል።

የፌዴሬሽኑን ምላሽ የያዘው ደብዳቤ ይህን ይመስላል፡-