ቻምፒየንስ ሊግ | ጅማ አባጅፋር ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ከጅቡቲው ቴልኮም ጋር የተገናኘው የአምናው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒየን ጅማ አባጅፋር በአጠቃላይ 5ለ3 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ የመጀመርያውን ዙር ተቀላቅሏል። በቀጣይም ከግቡፁ ኃያል አል አህሊ ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር ባሳለፍነው ሳምንት ጅቡቲ ላይ 3-1 ካሸነፈው ስብስብ በጉዳት ዛሬ ያልነበሩት ዘሪሁን ታደለ እና ዐወት ገ/ሚካኤልን በዳንኤል አጄይ እና ያሬድ ዘውድነህ ሲተካ ከድር ኸይረዲን እና መስዑድ መሐመድም በተስፋዬ መላኩ እና ኄኖክ ገምቴሳ ተተክተዋል።

09:56 የተጀመረው ጨዋታ ገና በመጀመሪያው ደቂቃ ነበር ግብ ያስተናገደው። በአባ ጅፋር ተጫዋቾች ስህተት የተገኘችውን ኳስ ተጠቅሞ መሐዲ ሁሴን ጅቡቲ ቴሌኮምን መሪ ያረገች ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡ በዚህቹ ግብ የተነቃቁ የሚመስሉት ጅብቲ ቴልኮሞች በድምር ውጤት ከአባጅፋር ጋር አቻ ሊያደርጋቸው የሚችለውን ተጨማሪ ግብ ለማግኘት በተለይ በመጀመመሪያዎቹ 20 ደቂቃዎች በፈጣን የመልሶ ማጥቃት ቶሎ ቶሎ ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል ለመድረስ ጥረት አድርገዋል። በ15ኛው ደቂቃ ላይ ፋቲአ አብዬደን በግንባር ገጭቶ የሞከራትና ለጥቂት ወደ ውጪ የወጣችበት ኳስም ለዚህ እንደማሳያ የምትቀርብ ሙከራ ነበረች፡፡

ጅማ አባ ጅፋሮች ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው በመመለስ 17ኛው ደቂቃ ላይ አቻ ሆነዋል። ዲዲዬ ለብሪ ከሳጥን ውጪ በቀጥታ ወደግብ የላካት ኳስ የጅብቲው ግብጠባቂ ሲተፋው በቅርብ ርቀት የነበረው ማማዱ ሲዴቤ የአቻነቱን ግብ ለማስቆጠር ችሏል፡፡ ማማዱ ሲዴቤ ባለፈው ሳምንት በተደረገው ጨዋታም ሁለት ጎሎች ማስቆጠሩ የሚታወስ ነው።

ከግቧ መቆጠር አንስቶ በቀሩት የመጀመርያ አጋማሽ ደቂቃዎች ባለሜዳዎቹ ጅማዎች በኳስ ቁጥጥር ረገድ የተሻሉ ነበሩ። ሆኖም በመስመሮች መካከል ሰፊ ክፍተትን ይተዉ የነበሩትን ጅብቲ ቴልኮሞችን አልፈው ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል፤ አጥቂው ማማዱ ሲዲቤም በግሉ ሁለት ጥሩ የሚባሉ ሙከራዎችን ማድረግ ችሏል፡፡ በ26ኛው ደቂቃ ኤልያስ አታሮ ወደ ቀኝ የተቃራኒ የግብ ክልል ጠርዝ ላይ የተገኘውን የቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ ልኮ ኳስዋ ከግቡ አናት በላይ ለጥቂት የወጣችበት ኳስም የመጀመሪያው አጋማሽ ሌላ ተጠቃሽ ሙከራ ነበር፡፡

ከእረፍት መልስ ተመጣጣኝ የሚባልና ጥሩ የመሸናነፍ ፉክክር የታየበት ነበር ፤ ሁለቱም ቡድኖች ቶሎ ቶሎ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በ54ኛው ደቂቃ ጅቡቲ ቴልኮሞች ያሻሙት የቅጣት ምት ምት ሲመለስ ጅማዎች በፈጣን ሽግግር ወደፊት በመጓዝ ይሁን እንደሻው አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ ዲዲዬ ለብሪ ቡድኑን ወደ መሪነት ያሸጋገረችበትን ጎል ማስቆጠር ችሏል።

በደቂቃዎች ልዩነት አባጅፋሮች የግብ ልዩነቱን ሊያሰፉበት የሚችሉበትን አጋጣሚ አግኝተው ኤልያስ አታሮ ከመስመር ያሻገረለትን ኳስ ማማዱ ሲዲቤ በግንባሩ በመግጨት ቢሞክርም የግቡ አግዳሚ ሊመልስበት ችሏል፡፡

በ70ኛው ደቂቃ የጅማው አምበል አዳማ ሲሴኮ በሰራው ጥፋት ጅቡቲ ቴሌኮሞች ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት ፋአቲ አቢአዶን መትቶ የጅማው ግብጠባቂ ዳንኤል አጄይ መመለስ ቢችልም የተተፋውን ኳስ ራሱ ፋአቲ አስቆጥሮ ዳግም የቡድኑ የማለፍ ተስፋ ላይ የተስፋ ጭላንጭል አሳይቶ ነበር፡፡

በቀሩት ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር ሳይችሉ ጨዋታው 2ለ2 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል። በዚህም መሠረት ጅማ አባጅፋር ባሳለፍነው ሳምንት ከሜዳ ውጪ ባስመዘገበው ድል ታግዞ በድምር ውጤት ቀጣዮን ዙር መቀላቀል ችሏል።

የአባ ጅፋር ቀጣዩ ተጋጣሚ የስምንት ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው የግብፁ አል አህሊ ነው። የመጀመርያው ጨዋታ ከታኅሳስ 5-7 ካይሮ ላይ ሲደረግ በሳምንቱ የመልሱ

ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ የሚከናወን ይሆናል። አል አህሊ በ2004 ኢትዮጵያ ቡናን የገጠመበት ጨዋታ ከኢትዮጵያ ክለቦች ጋር ያደረገው የመጨረሻ እርስ በእርስ ግንኙነት ነው።


የጨዋታውን ሙሉ መረጃ ሊንኩን ተጭነው ያገኛሉ ፡ LINK