የአሰልጣኞች አስተያየት| ጅማ አባ ጅፋር 2-2 ጅቡቲ ቴሌኮም

በ2018/19 የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ጅቡቲ አቅንቶ ጅቡቲ ቴሌኮምን 3ለ1 አሸንፎ የተመለሰው ጅማ አባጅፋር በዛሬው የአዲስ አበባ ስታዲየም የመልስ ጨዋታ 2ለ2 ተለያይቶ በድምር ውጤት 5ለ3 በማሸነፍ አንደኛውን ዙር ተቀላቅሏል፡፡ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች በዚህ መልኩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ዩሱፍ ዓሊ – ጅማ አባ ጅፋር (ረዳት አሰልጣኝ)

“ከመጀመሪያው ጨዋታ ይዘን የመጣነው ውጤት በተወሰነ መልኩ አዘናግቶናል፡፡ በተረፈ በአጠቃላይ ይዘነው ከመጣነው ውጤት አንጻር ጨዋታውን አቅልለን ለመጫወት ሞክረናል። በመጪው እሁድ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ስላለን ተጫዋቾች ለማሳረፍም ጥረት አድርገናል።”

ጅቡቲ ቴሌኮም

ጨዋታው መጥፎ የሚባል አልነበረም፤ ተጋጣሚያችን ጠንካራ ቡድን ነው፡፡ በመጀመርያው ጨዋታ 3ለ1 ተሸንፈናል። በሜዳችን ስንጫወት በሰው ሰራሽ ሳር ላይ ነበር፤ እዚህ ደግሞ የተፈጥሮ ሳር ላይ ነው የተጫወትነው፡፡ ወደ ዛሬው ጨዋታ ስንመጣ ቢያንስ የተወሰነ ጥሩ ነገር ይዘን መሄድ እንዳለብን አስበን ለማሸነፍ ነበር የመጣነው።