ደደቢቶች ከስምንት ቀናት በኋላ ወደ ልምምድ ተመልሰዋል

በደሞዝ ምክንያት ልምምድ አቋርጠው የነበሩት የደደቢት ተጫዋቾች ዛሬ 10:00 ላይ ወደ ልምምድ ተመልሰዋል።

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ልምምድ ካቆሙ በኋላ ላለፉት ስምንት ቀናት ከልምምድ ርቀው የነበሩት የደደቢት ተጫዋቾች ያልተከፈላቸው ደሞዝ በቅርብ ቀን ገቢ እንደሚሆንላቸው ቃል ተገብቶላቸው ወደ ልምምድ ተመልሰው እሁድ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ላላቸው ጨዋታ ዝግጅት ጀምረዋል።

ሶስት ጨዋታዎች አካሂደው በሶስቱም ተሸንፈው ነጥብ ማስመዝገብ ያልቻሉት ሰማያዊዎቹ  ከድሬዳዋ ጋር ላላቸው ጨዋታ ነገ ወደ ሐረር ያቀናሉ።