የከፍተኛ ሊግ ሶስተኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ተጀምሯል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ አንድ ጨዋታ ሲጀመር በነገው ዕለት በ17 ጨዋታዎች እንደሚቀጥል ይጠበቃል። 

ዛሬ ሶዶ ላይ በወላይታ ሶዶ ከተማ እና ድሬዳዋ ፖሊስ መካከል የተደረገው ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤተ ተጠናቋል። የመጀመርያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ አንድ ደቂቃ ሲቀረው ባለሜማዎቹ ሶዶዎች ፉዓድ አብዱ ባስቆጠረው ጎል ቀዳሚ መሆን ቢችሉም በ55ኛው ደቂቃ ፍፁም አቦነህ ድሬዳዋ ፖሊስን አቻ ማድረግ ችሏል። ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ሁለቱም ቡድኖች ከሁለት ጨዋታ ሁለት ነጥብ መያዝ ችለዋል።  

የነገ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው:-

ምድብ ሀ

እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2011

ለገጣፎ ለገዳዲ 09:00 ቡራዩ ከተማ

ወልዲያ 09:00 ገላን ከተማ

ወሎ ኮምቦልቻ 09:00 አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ

አውስኮድ 09:00 ደሴ ከተማ

አክሱም ከተማ 09:00 ሰበታ ከተማ

ፌዴራል ፖሊስ 10:00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ

ምድብ ለ

ቅዳሜ ኅዳር 29 ቀን 2011

ወላይታ ሶዶ ከተማ 1-1 ድሬዳዋ ፖሊስ

እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2011

የካ ክ/ከተማ 08:00 ነጌሌ አርሲ

ሀምበሪቾ ዱራሜ 09:00 ኢትዮጵያ መድን

አዲስ አበባ ከተማ 09:00 ወልቂጤ ከተማ

ሀላባ ከተማ 09:00 ዲላ ከተማ

ኢኮስኮ 09:00 ናሽናል ሴሜንት

ምድብ ሐ 

እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2011

ጅማ አባ ቡና 09:00 ካምባታ ሺንሺቾ

ካፋ ቡና 09:00 አርባምንጭ ከተማ

ስልጤ ወራቤ 09:00 ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ

ቤንች ማጂ ቡና 09:00 ሀዲያ ሆሳዕና

ቡታጅራ ከተማ 09:00 ነቀምት ከተማ

ሻሸመኔ ከተማ 09:00 ነጌሌ ከተማ