መቐለ 70 እንደርታ በመርሐ ግብር መቆራረጥ ዙርያ ቅሬታውን ገለፀ

መቐለ 70 እንደርታ ሊጉ መቆራረጡ ቡድኑን እየጎዳው መሆኑን በይፋዊ ደብዳቤ ገለፀ።

በዚህ ዓመት መጀመርያ ስያሜው ከመቐለ ከተማ ወደ መቐለ 70 እንደርታ በመቀየር በሊጉ ተከታታይ ጨዋታዎች አሸንፎ መልካም አጀማመር ያደረገው ክለቡ ፌደሬሽኑ ሁለት የሊግ  ጨዋታዎቹን ማዘዋወሩ በቡድኑ ወቅታዊ ውጤት እና የክለቡ ፋይናንስ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን ገልጿል። ከዚ በተጨማሪ ፌደሬሽኑ ክለቦች በየሜዳቸው እንዲጫወቱ የጀመረው ስራ እንደሚደግፍ እና ይህን የማይሆን ከሆነ ግን የዓለም አቀፍ ህጉን በተከተለ መልኩ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።