የካፍ ኮከቦች የመጨረሻ 10 እጩዎች ታውቀዋል

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የ2018 የአህጉሪቱ ኮከቦችን ጃንዋሪ 8 በሴኔጋሏ መዲና ዳካር ይመርጣል። ለዚህ ሽልማት የመጨረሻ እጩዎችንም በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።

በ11 የሽልማት ዘርፎች የሚካሄደው የዘንድሮው መርሐ ግብር በ2018 ነጠረው ለወጡ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች፣ ወጣት ተጫዋቾች፣ ቡድኖች በሁለቱም ጾታ እውቅና የሚሰጥ ሲሆን የዓመቱ ምርጥ የፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በታላቁ የእግርኳስ ሰው ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ስም ለመጀመርያ ጊዜ ይካሄዳል። የአፍሪካ ምርጥ 11 ከፊፋ ፕሮ ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ሲሆን በበይነ መረብ በሚሰበሰብ ድምፅ አማካኝነት የዓመቱ ምርጥ ጎል ሽልማትም ይከናወናል።


የወንዶች እጩዎች

አሌክስ ኢዎቢ (ናይጄርያ/አርሰናል)፣ አንድሬ ኦናና ( ካሜሩን/አያክስ)፣ ዴኒስ ኦኒያንጎ (ዩጋንዳ/ማሜሎዲ ሰንዳውንስ)፣ መሕዲ ቤናሺያ (ሞሮኮ/ጁቬንቱስ)፣ መሐመድ ሳላህ (ግብፅ/ሊቨርፑል)፣ ፔየር-ኤምሪክ አውባሚያንግ (ጋቦን/አርሰናል)፣ ሪያድ ማህሬዝ (አልጄርያ/ማን ሲቲ)፣ ሳዲዮ ማኔ (ሴኔጋል/ሊቨርፑል)፣ ዋሊድ ሶሊማን (ግብፅ/አል አህሊ)


የሴቶች እጩዎች

አብዱላይ ሙካራማ (ጋና/ኖርዘርን ሌዲስ)፣ አሲስት ኦሾአላ (ናይጄርያ/ዲሊያን ኳንጂያን)፣ ባሲራ ቱሬ (ማሊ/ኤኤስ ማንዴ)፣ ክሪስቲና ጋትላና (ደቡብ አፍሪካ/ሆስተን ዳሽ)፣ ኤልዛቤት አዶ (ጋና/ሲያትል ሬይን)፣ ፍራንሴስካ ኦርዴጋ (ናይጄርያ/ዋሺንግተን ስፒሪት)፣ ጋብሬል አቦዲ (ካሜሩን/ሲኤስኬኤ ሞስኮ)፣ ጃኔ ቫን ዊክ (ደቡብ አፍሪካ/ሆስተን ዳሽ)፣ ኦኖሜ ኤቢ (ናይጄርያ/ሔካን ሁዊሳንሀንግ)፣ ራይሳ ፊውዲጆ (ካሜሩን/አላንድ ዩናይትድ)፣ ታቢታ ቻዊንጋ (ማላዊ/ጂያንግሱ ሰኒንግ)


ወጣት ተጫዋቾች

አሽራፍ ሀኪሚ (ሞሮኮ/ቦሩስያ ዶርትሙንድ)፣ ፍራንክ ኬሲ (አይቮሪኮስት/ኤሲ ሚላን)፣ ዊልፍሬድ ንዲዲ (ናይጄርያ/ሌይስተር ሲቲ)


አሰልጣኝ (በወንዶች)

አሊዩ ሲሴ (ሴኔጋል)፣ ሔርቨ ሬናርድ (ሞሮኮ)፣ ሞይኔ ቻባኒ (ኤስፔራንስ ደ ቱኒስ)


አሰልጣኝ (በሴቶች)

ዴዚሪ ኤሊስ (ደቡብ አፍሪካ)፣ ጆሴፍ ብሪያን ንዶኮ (ካሜሩን)፣ ቶማስ ዴኔርቢ (ናይጄርያ)


ብሔራዊ ቡድን (በወንዶች)

ማዳጋስካር፣ ሞሪታንያ፣ ዩጋንዳ


ብሔራዊ ቡድን (በሴቶች)

ካሜሩን፣ ናይጄርያ፣ ደቡብ አፍሪካ