ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ የወድድር ዓመቱ የመጀመርያ ድሉን አስመዝግቧል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሦስተኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ አንድ ጨዋታ ሲጀመር ነገ በሚደረጉ 16 ጨዋታዎች ይቀጥላል። 

ዛሬ በነበረው ብቸኛ መርሐ ግብር ወደ ድሬዳዋ ያመራው ሀላባ ከተማ ድሬዳዋ ፖሊስን 3-2 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን የመጀመርያ ሦስት ነጥቦች ሰብስቧል። 

ካሳሁን ገረመው በ37ኛስ ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ቀዳሚ መሆን የቻሉት ሀላባዎች በ58ኛው ደቂቃ በኤፍሬም ቶማስ እንዲሁም በ62ኛው ደቂቃ በአብዱልዓዚዝ ዑመር ጎሎች ልዩነቱን ወደ ሦስት አስፍተዋል። ከአንድ ደቂቃ በኋላ ካሌብ አበበ ልዩነቱን ወደ ሁለት ሲያጠብ ዘርዓይ ገብረሥላሴ በ88ው ደቂቃ ተጨማሪ ጎል አስቆጥሮ ባለሜዳዎቹን በመጨረሻ ደቂቃ አቻ ለማድረግ ቢቃረብም ተጨማሪ ጎል ሳይስተናገድ ጨዋታው በሀላባ ከተማ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል። 

በውጤቱ መሠረት ሀላባ ከተማ ከሦስት ጨዋታዎች 5 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሌሎቹ የምድቡ ቡድኖች ጨዋታቸውን ከማድረጋቸው በፊት በመሪነት ላይ ተቀምጧል። 

የነገ ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-


ምድብ ሀ
እሁድ ታኅሳስ 7 ቀን 2011
ኢትዮ ኤሌክትሪክ 09:00 አውስኮድ
ሰበታ ከተማ 09:00 ፌዴራል ፖሊስ
አቃቂ ቃሊቲ 09:00 አክሱም ከተማ
ገላን ከተማ 09:00 ወሎ ኮምቦልቻ
ቡራዩ ከተማ 09:00 ወልዲያ
ደሴ ከተማ 09:00 ለገጣፎ ለገዳዲ
_____

ምድብ ለ
ቅዳሜ ታኅሳስ 6 ቀን 2011
ድሬዳዋ ፖሊስ 2-3 ሀላባ ከተማ
እሁድ ታኅሳስ 7 ቀን 2011
ዲላ ከተማ 09:00 ኢኮስኮ
ወልቂጤ ከተማ 09:00 ወላይታ ሶዶ ከተማ
ነጌሌ አርሲ 09:00 አዲስ አበባ ከተማ
ኢትዮጵያ መድን 09:00 የካ ክ/ከተማ
ናሽናል ሴሜንት 09:00 ሀምበሪቾ ዱራሜ
_____

ምድብ ሐ
እሁድ ታኅሳስ 7 ቀን 2011
ነጌሌ ቦረና 09:00 ካፋ ቡና
ነቀምት ከተማ 09:00 ሻሸመኔ ከተማ
ሀዲያ ሆሳዕና 09:00 ቡታጅራ ከተማ
ቢሾፍቱ አውቶ. PP ቤንች ማጂ ቡና
ካምባታ ሺንሺቾ 09:00 ስልጤ ወራቤ
አርባምንጭ ከተማ 09:00 ጅማ አባ ቡና
_____