የፕሪምየር ሊጉ ተስተካካይ ጨዋታዎች በከፊል ቀጣዩ ሳምንት ላይ ይደረጋሉ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይከናወኑ ወደ ሌላ ጊዜ ከተሸጋገሩ 13 ጨዋታዎች መካከል ገሚሱ በተስተካካይ መርሐ ግብር የሚካሄዱበትን ጊዜ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ቀን የተቆረጠላቸው ተስተካካይ መርሐ ግብሮች የሚከተሉትን ይመስላሉ

ረቡዕ ታኅሳስ 17 ቀን 2011

09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ደቡብ ፖሊስ (ሐረር)

09:00 ባህር ዳር ከተማ ከ ስሑል ሽረ (ባህር ዳር)

09:00 መቐለ 70 እ. ከ ፋሲል ከነማ (መቐለ)

11:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ወልዋሎ ዓ/ዩ (አአ)

ሐሙስ ታኅሳስ 18 ቀን 2011

09:00 ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና (ሶዶ)

11:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ጅማ አባ ጅፋር (አአ)

የተስተካካይ ጨዋታዎቹ ረቡዕ እና ሐሙስ ከተደረጉ በኋላ የስምንተኛ ሳምንት መደበኛ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ እንደሚቀጥሉ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።