አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ መልቀቂያ አስገብተዋል

አዲሱን የውድድር ዓመት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር የጀመሩት አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ባስገቡት ደብዳቤ ከክለቡ ጋር መለያየታቸው እርግጥ ሊሆን ተቃርቧል።

ትናንት ባስነበብነው ዜና መሰረት ከአዲሱ ክለባቸው ድሬዳዋ ከተማ ጋር የመዝለቃቸው ጉዳይ አጠራጣሪ ሆኖ የነበረው የአሰልጣኝ ዮሀንስ ሣህሌ ጉዳይ ሊለይለት ተቃርቧል። የምስራቁ ክለብ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ከአንድ ሰዓት በፊት እንዳስታወቀው አሰልጣኙ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተረጋግጧል።

“ለክለቡ በደረሰ ደብዳቤ መሰረት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ውላቸውን ለማቋረጥ መገደዳቸውን አሳውቀውናል” በሚለው የክለቡ የፌስቡክ መግለጫ መሰረት ባደረግነው ማጣራት በሁለቱ አካላት መካከል ባለው ስምምነት መሰረት ጥያቂያቸው ተቀባይነት አግኝቶ በውሉ ዝርዝር ጉዳይ ላይ ከተወያዩ በኋላ በይፋ እንደሚለያዩ ይጠበቃል።

በመሆኑም ክለቡ ነገ ሶዶ ላይ ከወላይታ ድቻ የሚያደርገው የስምንተኛ ሳምንት የሊግ ጨዋታ ላይ ምክትል አሰልጣኝ ስምዖን አባይ ቡድኑን እየመሩ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበበቃል።